Ecclesiastes 3:14: I know that everything God does will endure forever; nothing can be added to it and nothing taken from it. God does it so that people will fear him.

Yordanos & Yabets

August 30, 2025
82 Days To Go!

Ecclesiastes 3:14: I know that everything God does will endure forever; nothing can be added to it and nothing taken from it. God does it so that people will fear him.

Yordanos & Yabets

August 30, 2025
82 Days To Go!

Our Story In Amharic(የኛ ታሪክ)

የዮርዳኖስ እና የያቤፅ ታሪክ

ትርጉም ፡ ሽልማት ተሰማ


በጸሎት እና በዓላማ ላይ የተመሰረተ ፍቅር


ተራኪ ፋና ተክሌ


ጅማሬው የእግዚአብሔር መገኘት በሙላት በሚታይበት ልዑሉ በሚመለክበት ህብረቷ ጠንካራ በሆነባት የተቀባ የእግዚአብሔር ቃል ቤተክርስቲያን (AWGC) ውስጥ ነበር። ይህች ቤተ ክርስቲያን የመንፈስ ቅዱስ መገኘት ያለባት፣ ጸሎት፣ አምልኮ፣ ስብከት፣ መንፈሳዊ አገልግሎት የሚካሄድባት ቤተ ክርስቲያን ናት። በዚህ ስፍራ የህይወት ታሪካቸው ጀመረ፡፡


ያቤፅ ተሰጥኦ ያለው ሙዚቀኛ ሲሆን ከልቡ እግዚአብሔርን የሚያገለግል ሁል ጊዜ ቀድሞ በቤተክርስቲያን በመገኘት መድረኩን በማዘጋጀት፣ የሙዚቃ መሳሪያዎችን በማስተካከል በእለቱ ከሚያገለግሉን ዘማሪዎች ጋር መዝሙሮችን እየተለማመደ ሙዚቃን በመቃኘት በአገልግሎቱ ላይ የሚያተኩር የተሰጠ አገልጋይ ነው፡፡


በሌላ በኩል ዮርዳኖስ በእግዚአብሔር ቤት መገኘት አለሟ የሆነ፤ ጌታን የምትወድ የሷ አለም ደስታና የነፍሷ እርካታ ያለው ፀሎቷ ጋር የሆነ የምትወደድ ልጅ ናት፤ በቤተክርስቲያን ውስጥ ፀሎት በመምራት የምታገለግል፤ ከዋናው ፕሮግራም በፊት የጠዋቱን የጸሎት አገልግሎት በታማኝነት ትከታተል ነበር በዚህ ሁሉ ውስጥ ግን እግዚአብሔር ለሰው በማይታይ መልኩ አንድ አስገራሚ እና ውብ ነገር እያቀናበረ መሆኑን በፍፁም አታውቅም ነበር፡፡


በአንድ አይነት ስፍራ፣ በአንድ ልብ እና በአንድ መንፈስ እግዚአብሔርን እያመለኩ ሳምንታቶች ነጎዱ


በ2023 የአዲስ አመት የቤተክርስቲያን ፐሮግራም ላይ አንድ የማይረሳ አጋጣሚ ተፈጠረ። መንፍስ ቅዱስ በሞላብት በዚያ የቤተክርስቲያን አዳራሸ ከአምልኮ በኋላ ዮርዳኖስ ግጥም ለማንበብ ወደ መድረኩ ወጣች በዚያም ጊዜ ያቤፅ ከዚህ በፊት ያውቃት የነበረ ሰው አይነት ስሜት ተሰማው በምታነብበት ጊዜ የእሷ ድምፅ ብቻ አልነበረም፤ ሰላም ነበረ፣ ጸጋ ነበረ፣ ቅባት ነበረ ይቺ ሴት ያንተ ነች ይሚል አይነት ድምፅ በአይምሮ ውስጥ አቃጨለ። በዛም ቅፅበት ያቤፅ ልብ ውስጥ ዘር ተዘራ አንድ ቀን ሚስቱ እንደምትሆን የሚያስረዳ።


ይሄም ዘር አንድ እሁድ ከአገልግሎት በኋላ ፣ ከፓስተር ሚኪ፣ ከገኒ (የዮርዳኖስ እህት) እና ከያቤፅ ጋር በተደረገ የምሳ ግብዣ ላይ ብቅ ማለት ጀመረ። ቀለል ያለ ሳቅ እና ጨዋታ የተሞላበት ደስ የሚል ጊዜ ነበር። ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር በጣም የተለመዱ ሁኔታዎች ውስጥ ድንቅ ነገሮችን ለመጀመር ይንቀሳቀሳል።


ከጥቂት ጊዜ በኋላም ያቤፅ የዮርዳኖስን ስልክ ቁጥር ጠየቀ እና ለእራት ግብዣ ቀጠራት፤ ነገር ግን በተለያዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶች፣በስራ እና ሌሎች ጉዳዮች ምክንያት የእራት ቀጠሮው በተደጋጋሚ ተላለፈ።


በመጨረሻም ሴፕቴምበር 2023 ተገናኙ። የመጀመሪያው የእራት ቀጠሮ። ስለሕይወት ፣ ስለእምነት ፣ ስለዓላማ ... ሁሉንም ተጨዋወቱ ። በኋላ ያቤፅ ዮርዳኖስ የቸኮለች መሰለውና በፍጥነት ለመውጣት የፈለግሽ ትመሲያለሽ አላት እውነቱን ለመናገር እሷ ምንም የችኮላ ስሜት አልነበራትም ይልቁንም ትክክለኛ እና በቂ ጊዜ ፈገግታ የተሞላበት ቅንነት የታየበት ጥልቅ ስሜት የነበረበት መልካም እና በቂ ቆይታ እንደነበራት ነው የተሰማት፡፡



ከዚያ በኋላ ሁለቱም በተለያየ የህይወት መስመር ተጓዙ ወራቶች አለፉ ወቅቶች ተለዋወጡ


ከአንድ አመት ገደማ በኋላ፣ ያቤፅ በድጋሚ ዮርዳኖስን በፓስተር ሀንፍሬ የምስጋናና የአድናቆት ስርአት ላይ ተወዳጅዋ ዘማሪ ሊሊ እንደምታገለግል ነግሮዋት ፕሮግራሙ ላይ እንድትገኝ ቢጋብዛትም መገኘት አልቻለችም። ነገር ግን አጋጣሚው እግዚያብሔር በልባቸው የጀመረውን ሃሳብ የሚያስቀጥልብትን ሌላ እድል እንደገና ከፈተ።


ብዙም ሳይቆዩ በኖቬምበር 2024 እራት ጋበዛት፤ ይሄኛው ጊዜ ከባለፈው ከፍ ያለ የተለየ ድባብ የነበረው፤ ደስታ፣ እና ጥልቅ ስሜት የነበረው መሆኑን ሁለቱም በመንፈሳቸው ሰላም አውቀዉታል፣ አዎ ደስ የሚል በልብ ውስጥ የሚፈስ ሰላም ነበረው፤ ዓላማውን ያገኘ ትክክለኛ የህይወት ጉዞ ተሰምቷቸዋል ።


ግንኙነቱ እያደገ መሆኑ ስለገባቸው ሁለቱም ተስማምተው በአንድ ላይ እግዚአብሔርን ለመፈለግ ጊዜው አሁን እንደሆነ ስላወቁ እግዚአብሔር ማረጋገጫ እና አቅጣጫ እንዲሰጣቸው በህብረት መፀለይ ጀመሩ ለሦስት ተከታታይ ቀናት፣ ከአርብ እስከ እሁድ፣ ፆም እና ፀሎት ጀመሩ ስለ ግንኙነታቸው ብቻ ሳይሆን መልካም የሆነውን ፈቃዱን ለማወቅ መፀለያቸውን ቀጠሉ፡፡


በመጨረሻዋ ቀን ማለትም እሁድ በሶስተኛው ቀን በአካል ተገናኝተው እርስ በርሳቸው እጅ ለእጅ ተያይዘው ጸለዩ፥


መክብብ 3:14 "እግዚአብሔር ያደረገው ሁሉ ለዘላለም እንዲኖር አወቅሁ፤ ሊጨመርበት ወይም ከእርሱ ሊጐድል አይቻልም፤ እግዚአብሔርም በፊቱ ይፈሩ ዘንድ አደረገ።" መንፈስ ቅዱስ በጓደኝነታቸው መካከል ሦስተኛው ገመድ እንዲሆን ጋበዙት።


ከዚያም ጊዜ ጀምሮ የጋራ ጸሎት የተለመደ ሆነ። ከንጋቱ 3 እስከ 5 ባለው ሰአት መካከል በጋራ በስልክ ይጸልያሉ፣ ቃሉን ያነባሉ፣ በዚህም በመንፈሳዊውም በግኑኘነታቸውም ማደግ ሆነ። ምንም እንኳን አንዳንድ ጊዜ በሥራ እና ህይወት የፀሎት ልምዳቸውን ቢስተጓጎልም የልብ ፍላጎታቸው ግን ጠንካራ ነው ::


በፌብርዋሪ 14,2025 ለሁለት ቀን የሚሆን ጊዜን ለማሳለፍ ከColumbia, MD ለሶስት ሰአታት ያክል በመንዳት ወደ Calvary Campground in Ashland, Virginia አመሩ። ትኩረትን ሰብስቦ የሚያስተጓጉል ነገር ሳይኖር ለመጸለይ፣እግዚአብሔርን ለመፈለግ እና ወደኋላ የሚጎትትን ነገር ለመስበር አዲስን ነገር ወደ ህይወታቸው ለመጋበዝ ነበር።


Calvary Campground (የቀራኒዮ ካምፕ) ለዓመታት በአምልኮ፣ በጸሎት፣ የተለያዩ መንፈሳዊ ኪሩሴዶች የሚካሄድበት እና የመንፈስ ቅዱስ እሳት የሞላበት ቦታ ነው። ወደ ግቢው ሲገባ የእግዚአብሄር ክብር በዚያ ስፍራ እንዳለ ታስተውላላችሁ፡፡ በዚያን እለት የእለቱ ፕሮግራም እየተካሄደ ነበር፡፡ እነርሱም ወደ አምልኮው ስፍራ ገብተው በእግዚአብሄር ፊት ጮሁ፣ ጸለዩ ፣ተግዳሮት ተሰበረ ፣ አመለኩ ፣ መልካምንም ጊዜ በዚያን ስፍራ እግዚአብሄር ሰጣቸው ፣ ሰላምም በውስጣቸው እንደ ወንዝ ፈሰሰ፡፡


ነገሮች እንደቀድሞው አልነበሩም፣ ቀለላቸው፣ ወደ እግዚአብሔርም እርስ በርሳቸውም በይበልጥ ተቀራረቡ፡፡ይህም ጥሶ በመውጣት፣ በእምነት፣ በድል ፣ በኪዳን ፣በሰማያዊ በሆነ ድምፅ "የገቡበት" መንገድ ነው ። እግዚአብሔር ለልባቸው ተናገረ። ይህም በሕይወታቸው ውስጥ መለኮታዊ ምልክት ሆነ፡፡


ትኩረትን ከሚከፋፍሉ ከህይወት ጫጫታ ለጥቂት ጊዜ ለመራቅ፣መንፈሳዊ የጥሞና ጊዜ ለማሳለፍ ጥማት ወይም ረሃብ ካለህ እንዲሁም የህይወት አቅጣጫዎችን ለመቅበል በአንድ ልብ እና ሃሳብ ለጥቂት ጊዜ ለመቆየት እጅግ በጣም መልካም የሆነ ስፍራ ነው፡፡ ለህይወት ፈውስ ፣ አዲስ ነገር ለመጀመር ፣ የህወትን መንገድ ለማወቅ በጥሞና፣ ትኩረትን እና ሃሳብን ሰብስቦ በእግዚአብሄር ፊት በመሆን የእግዚአብሔር ድምጽ ለመስማት Calvary Campground (የቀራኒዮ ካምፕ)በጣም የተመቻቸ ቦታ ነው።


እነዚያ ሁለት የጸሎት ቀናት ፦ ጥያቄዎች በነበራቸው ሁኔታ ላይ መልስን ። ርቀት የነበረበት ሁኔታ ላይ አንድነትን አመጣ።የእግዚአብሔርም ፍቃድ ሁሉ በልባቸው አረጋገጡ። ይህም በእግዚአብሄር የታቀደ እና የተጀመረ የፍቅር ታሪክ ሆነ ።


ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ፣እርምጃቸው ታላቅ እምነት የተሞላበት ሆነ። በችኮላ ሳይሆን በእርጋታ። በፍለጋ ሳይሆን መልህቅ በመሆን። ጸሎታቸው ወደ ታላቅ መለኮታዊ እቅድ እና አላማ ፣ መጠባበቃቸውም ወደ አንድነት እና መዘጋጀት የለወጠ አምላክ እና አባታችን ጌታ እየሱስ ክርስቶስ ስሙ ከዘላለም እስከ ዘላለም ይክበር አሜን!!!።


የእግዚአብሔር ጊዜ ሁልም ትክክል ነው!!!


እናማ በኦገስት 30 2025 ዮርዳኖስ እና ያቤፅ በእግዚአብሔር ፣ በቤተሰቦቻቸው እና በጓደኞቻቸው ፊት ቆመው እጅ ለእጅ ተያይዘው ቃልኪዳን ይገባሉ።


ይህም ቀን መልካም ያደረገልልን እግዚአብሔርን በአምልኮ፣ በምስጋና የምናመሰግንበት ቀን ይሆናል።


መክብብ 3:11

ነገርን ሁሉ በጊዜው ውብ አድርጎ ሠራው፤ እግዚአብሔርም ከጥንት ጀምሮ እስከ ፍጻሜ ድረስ የሠራውን ሥራ ሰው መርምሮ እንዳያገኝ ዘላለምነትን በልቡ ሰጠው።


በእግዚአብሔር ቤት የተጀመረ፣ በጸሎት የተመሠረተ፣ ለእግዚአብሔር ምስጋና ለማምጣት፣ ለማደግ፣ እና ለማመጨመር የተዘጋጀ የፍቅር አንድነት ሆነ።